ሐኪም ማማከር ያለብኝ መቼ ነው?

የጠዋት ህመምዎ ቀንም ሌሊትም ከቆየ ሰውነትዎ በቂ ንጥረ ነገርና ፈሳሽ ላያገኝ ይችላል። በተጨማሪ ለእርስዎና ለጽንሱ የሚያስፈልጉትን ቫይታሚኖችና ሚኒራሎች ሰውነትዎ ላያገኝ ይችላል። በእርግዝና ወቅት ብዙ ሴቶች ክብደት ይቀንሳሉ ወይም ተገቢውን ክብደት አይጨምሩም። አስቸጋሪ የጠዋት ህመም ሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም ወይም ፈሳሽ ማጣትና የተመጣጠነ ምግብ ማጣትን ሊያስከትል ይችላል።

ጥሩው ዜና ከባድ ማቅለሽለሽና ማስታወክ ቢኖርዎት እንኳ ተገቢውን አካሄድ ከተከተሉና ካስፈለገም አግባብነት ያለው ህክምና ከተገኘ እርስዎንና ማህጸን ውስጥ ያለው ጽንስ ሊደርስበት ከሚችለውን ጉዳቶች መከላከል መቻሉ ነው።

דאגה מבחילות והקאות בהיריון

ህክምና እንደሚያስፈልግ የሚመከረው መቼ ነው?

ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱ ወይም ከዛ በላይ ከታየ፦

  • በ24 ሰዐታት ውስጥ መብላት ወይም መጠጣት ካልቻሉ ወይም ማንኛውም የበሉት ወይም የጠጡትን ካስታወኩ።
  • መድከም ወይም መዛል ከተሰማዎት።
  • አፍዎና ከንፈርዎ ከደረቀ።
  • ትንሽ፣ ጠቆር ያለና ጠንካራ ሽታ ያለው ሽንት ካለዎት።
  • ተገቢውን ክብደት ካልጨመሩ ወይም ክብደት ከቀነሱ (ከ1-2 ሳምንታት ውስጥ 2.5 ኪሎ ገደማ ከቀነሱ)።

የሚመረምርዎትና ያጋጠምዎትን ማቅለሽለሽና ማስታወክ እንዴት እንደሚቋቋሙት የሚመክርዎት ሀኪም ይዩ። አንዳንድ ሴቶች በደም ስር የሚገባ ፈሳሽ ቶሎ ቶሎ ያስፈልጋቸዋል። ይህ ህክምና በአብዛኛው የሚደረገው ሆስፒታሉ ውስጥ ነው።