ለጤናማ እርግዝና ምክሮች፦ ለሚቀጥለው እርግዝና ምን ማድረግ አለብኝ?

በሚቀጥለው እርግዝናዎ ላይ ብዙ የጠዋት ህመምና ሃይፐርሚስስ ግራቪዳረም በድጋሚ የመከሰት ከፍተኛ እድል (75-85%)ስላለ መዘጋጀቱ ጥሩ ነው። የአመጋገብና የአኗኗር ሁኔታዎን ለውጥ ማርገዝ ሲያስቡ ጀምረው ወይም ማርገዝዎን እንዳወቁ ወዲያው መጀመር አለብዎት። በቀድሞው እርግዝና (እርግዝናዎች) ብዙ የጠዋት ህመምና ሃይፐርሚስስ ግራቪዳረም ከነበረዎት የማቅለሽለሹና ማስታወኩ ምልክቶች ከመጀመራቸው በፊት ወይም ወዲያው እንደጀመሩ ሙያዊ መረጃ ለማግኘት የማህጸን ሀኪምዎን ያማክሩ።  በሀኪምዎ የታዘዘውን ህክምና መተግበር በቶሎ ከጀመሩ ምልክትዎን በተሻለ ያድናል፣ ከመባባስ ይከላከላል እንዲሁም በእርግዝናዎ የህይወት ጥራትዎን ያሻሽላል።

משפחה עם הריון

በእርግዝና የመጀመሪያ ወቅት ወይም ሲያቅዱ የሚከተሉት ምክሮች ጠቃሚ ናቸው፦

  • የስኳር መጠን፦ የደም ስኳር መጠን ስለመስተካክል ይጠንቀቁ። በየ ከ1 እስከ 2 ሰዐታቱ ማንኛውም የገንቢ ምግብ ምንጭ እያንዳንዱ ምግብና ማቆያ (ስናክ) ውስጥ በመጨመር ትንሽ ምግብ ይመገቡ። የደም ስኳር መጠን ለማስተካከል፣ የጠዋት ህመም ምልክቶችን ለመቀነስና የልብ ማቃጠልና ሪፍለክስን (ጋስትሮኤሶፋጊያል ሪፍለክስ በሽታ፣ ምግብ ከጨጓራ ወደ ጉሮሮ ተመልሶ “ከፍ የሚልበት” ሁኔታ ) ለማብረድ ይረዳል።
  • ፈሳሽ፦ ቀስ እያሉ የእለት እለት ፈሳሽዎን ወደ 2 ሊትር ይጨምሩ። ከመጠጣት ባሻገር ከበረዶ የሚሰሩ ጣፋጭ ከረሜላዎችን፣ በረዶ፣ ወይም ከቀለጠ በረዶ የሚሰሩ ጣፋጭ መጠጦችን የፍራፍሬና አትክልት ስሙዚ አመጋገብዎ ላይ መጨመር ይችላሉ።
  • የስፖርት መጠጦች ወይም የቫይታሚን ውሀ በመጠጣት ጨው (ኤሌክትሮላይት) ስለመጨመር አስፈላጊነት ሀኪምዎን ያማክሩ።
  • ቫይታሚን ስለመውሰድ የማህጸን ሀኪምዎን ያማክሩ።
  • በቀድሞ እርግዝና ሀይፐርሚስስ ግራቪዳም ከነበርዎት ለሄሊኮባክተር መመርመር እንዳለብዎት ሀኪምዎን ይጠይቁ። ከአደገኛ የጠዋት ህመም ጋር ስለሚያያዝ ምርመራው መደረግ ያለበት ከማርገዝዎ በፊት ወይም በእርግዝናው መጀመሪያ ላይ ነው። ካለብዎት ይህን የባክቴሪያ መመረዝ መታከሙ ይጠቅማል።
  • የጠዋት ህመም የሚያስከትሉ ምክንያቶች ወይም የሚያባብሱትን ይጠንቀቁ። ከማርገዝዎ በፊት ወይም በእርግዝናው መጀመሪያ ላይ አስቀድመው ስለመፍትሄው የማህጸን ሀኪምዎን ያናግሩ።
  • ለጠዋት ህመም የህክምና አማራጮች የማህጸን ሀኪምዎን ያናግሩ።
  • በእርግዝናው መጀመሪያ ላይ የልብ ማቃጠል፣ የአሲድ ሪፍለክስ (ጋስትሮኤሶፋጊያል ሪፍለክስ በሽታ) ወይም የምግብ አለመፈጨት ከጀመረ እባክዎን የአሲድ ምልክቶችን ለመቀነስ ምክሮች ይከተሉና ሀኪምዎን ያናግሩ።
  • እርዳታ፦ ከባለቤትዎ፣ ጓደኞችዎና ዘመድዎ እርዳታ ይጠይቁ። ምግብ ማን እንደሚሰራልዎት ያስተውሉ፣ የተሰራ ምግብ ይግዙ፣ እራስዎ ይገዛዙ፣ ስለቤት አያያዝ ሂደት ወይም ልጆች እርዳታ ያግኙ። እንደዚህ የተጣመረ እርዳታ በጣም ይረዳዎታል።