በእርግዝና ወቅት ማቅለሽለሽና ማስታወክን የሚያባብሱ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

በእርግዝና የጠዋት ህመም የአደገኝነት መጠን ከሴት ሴት ይለያያል። በእርግዝና ወቅት ማቅለሽለሽና ማስታወክን ብዙ ምክንያቶች ሊፈጥሩት ወይም ሊያባብሱት ይችላሉ።

የሚከተሉት ምክንያቶች ከአስቸጋሪ የእርግዝና ጊዜ ማቅለሽለሽና ማስታወክ ጉዳዮች ጋር የተገናኙ ናቸው፦

 • ብዙ ጽንሶች ያለው እርግዝና (መንታ፣ ሶስት ልጅ)
 • ትልቅ የእንግዴ ልጅ
 • የሞላር እርግዝና (ጥቂት፣ ያልተለመደ፣ እድገት የሌለው እርግዝና)።
 • የታይሮይድ እጢ መዛባት- የእጢው እንቅስቃሴ ባልተለመደ ሁኔታ መጨመር ወይም መቀነስ (ሀይፐርታይሮይዲዝም ወይም ሀይፖታይሮይዲዝም)።
 • የምግብ መንሸራሸር መዛባት ለምሳሌ የልብ መቃጠል ፣ ሪፍሌክስ፣ የክሮን በሽታ፣ አልሰሬቲቭ ኮላይተስ፣ ጋስትራይትስ፣ አልሰር።
 • የአዕምሮ ሁኔታ ለምሳሌ ጭንቀትና ድብርት ወዘተ።
 • የቫይረስ ወይም ባክቴሪያ መመረዝ ለምሳሌ ሳል፣ ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ የሽንት ትቦ መመረዝ፣ የሳይነስ መመረዝ፣ የጆሮ መመረዝ ወዘተ።
 • ቶሎ ቶሎ የሚከሰት ማይግሬን ወይም ራስ ህመም
 • በሄሊኮባክተር ፓይሎሪ ባክቴሪያ ሚመጣ መመረዝ
 • የስኳር በሽታ ወይም የእርግዝና ጊዜ የስኳር በሽታ
 • ከመጠን ያለፈ ውፍረት
 • ከፍተኛ የደም ግፊት
 • ያልታከሙ የህክምና ሁኔታዎች

ብዙ እርግዝናዎችን ያሳለፉ ሴቶች የበለጠ የመሰቃየት አዝማሚያ አላቸው። ከማስታወክ ጋርም ሆነ ያለማስታወክ ማቅለሽለሽ ያላቸው ወይም በቀድሞ እርግዝናዎች ሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም የሆኑ ሴቶች በወደፊት እርግዝናዎች የጠዋት ህመም አስቸጋሪ ሁኔታ ለመሰቃየት 75%-80%  አደጋ ላይ ናቸው። ስለዚህ የቀድሞ ልምድ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ እና/ወይም ምንም ሳይኖር በራስ ማስወጣትን ለመቋቋም ቀላል አያደርገውም።

የጠዋት ህመም የተለያዩ ጣእሞችና ጠረኖች ባሉበት ሊባባስ ይችላል። በሰውነት ውስጥ ሊፈጠሩ በሚችሉ የሆርሞን ለውጦች ምክንያት በእርግዝና ወቅት አንዳንድ ሴቶች መራራ፣ ኮምጣጣ ወይም የብረት ጣዕም በአፋቸው ውስጥ ይሰማቸዋል። አፋቸው ውስጥ የሚሰማቸው እንግዳ ስሜት ከመጠጣት ሊከለክላቸው ይችላል፤ ይህ ደግሞ ፈሳሽ ማጣትን ያስከትላል። ቀዝቃዛ ውሀ ወይም ማንኛውም ቀዝቃዛ መጠጥ መጠጣት እንዲሁም ማስቲካ ወይም ጠንካራ ከረሜላ ማኘክ ይረዳል።

בחילות בהיריוןበተጨማሪ ሴቶች በእርግዝና ወቅት ለጠረኖችና ሽታዎች የበዛ ንቁ ስሜት ያዳብራሉ። በዚህ ወቅት ሴቶች በአካባቢያቸው ላሉት ጠረኖችና ሽታዎች የበለጠ ትኩረት ይሰጣሉ እንዲሁም ጠንክረው ይሰሟቸዋል። በእርግዝናው ወቅት የተወሰኑ ሽታዎች ማቅለሽለሽ፣ የማስታወክ ስሜት እና/ወይም በእርግጥ ማስታወክን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ይህን ለማስወገድ በተዘጉ ክፍሎች ውስጥ መሆንን ማስወገድ፣ በተቻለ መጠን አካባቢን አየር እንዲያገኝ ማድረግና ቀዝቃዛ ምግብ ወይም ከትኩስ ምግብ ይልቅ የተለመደ የሙቀት መጠን ያለው ምግብ መመገብ ይመረጣል።