በእርግዝና ወቅት ከማቅለሽለሽና ማስታወክ ሌላ ተጨማሪ ምልክቶች

በእርግዝና ወቅት በጠዋት ህመም፣ ማስታወክ ቢኖርም ባይኖርም የሚሰቃዩ ብዙ ሴቶች እንደ ልብ ማቃጠል፣ የምግብ መንሸራሸር፣ የሆድ ድርቀትና ሌላም ባሉ ምልክቶች ሊሰቃዩ ይችላሉ። አንዳንዶቹ እነዚህ ምልክቶች ለጠዋት ህመሙ ሁኔታ አስተዋጽኦ ሊኖራቸው ይችላል።

ማቅለሽለሽና ማስታወክን እንደሚያባብስ የሚታወቀው በጣም የተለመደው ሁኔታ ቃር በመባል የሚታወቀው ነው፤ ይህ አንዳንዴ ጨጓራ ውስጥ ያለው ነገር ተመልሶ ወደ ጉሮሮ የሚመለስበት ጋስትሮኤሶፋጊያል ሪፍለክስ በሽታን (ሪፍለክስ) ያመጣል። ጨጓራ ውስጥ ያለው ነገር አሲዳማ ስለሆነ ቃር፣ ማግሳትና ማቅለሽለሽ ስሜት ሊፈጥር ይችላል። ቃርና ሪፍለክስ ህክምና የሚሰማዎትን ሁኔታ ሊያሻሽልና የጠዋት ህመም ምልክቶችን ሊያቀል ይችላል።
תופעות נוספות בהיריון የልብ ማቃጠልና ሪፍለክስ እንዴት መከላከል ወይም ማቃለል ይቻላል? የሚከተሉት ምክሮች ሊረዱ ይችላሉ፦

  • ለማረፍ ወይም ለመተኛት ጋደም ሲሉ የላይኛው ሰውነትዎንና ራስዎን በትራስ ወይም ከፍ ያድርጉ ወይም ቁልቁለታማነትን ለመፍጠር ፍራሹን ከፍ ያድርጉ ።
  • ከ1-2 ሰዐታት ውስጥ ትንሽ ትንሽ ለመመገብ ይሞክሩ። ጨጓራ ውስጥ አሲዳማነትን ለመቀነስ እያንዳንዱ ምግብዎ ውስጥ ገንቢ ምግብ ይጨምሩ።
  • ሲበሉ አይጠጡ። ከመብላትዎ በፊት ወይም ከበሉ በኋላ ከ20-30 ደቂቃ በኋላ ይጠጡ።
  • የቅባታማ ምግብ አጠቃቀምዎን ይቀንሱ።
  • ብዙ መመገብ ወይም የአመጋገብ ተራን መዝለል ያስወግዱ።
  • የምግብ መንሸራሸርን ለመጨመር በተቻለ መጠን ከምግብ በኋላ አጭር ጉዞ ያድርጉ።
  • ከተመገቡ በኋላ ወዲያው ጋደም አይበሉ።
  • ፕሮባዮቲክና የተለያዩ ምግብን የሚፈጩ ኢንዛይሞችን የያዙ ምርቶችና ምግቦች ሊረዱ ይችላሉ።
  • ቃርን ስለማከም ያለዎትን አማራጮች የማህጸን ሀኪምዎን ያማክሩ።